መንፈዐት ሐበት-አሰውዳ
ብዝሓም አንፋር ዲብ ውላድ ልግባእ ወአዋልድ ደረጀት ሸንሀት ጅማዕ ድህርት ለቦም ህለው።እሎም አንፋር እሎም ህዬ እት ው’ላድመ መሻክል እግል ለሀሌ እግሎም ቀድር። እብ ፍንቱይ ሸንሀት ጅማዕ ለአለቦም አውመ ድሁር ቅያስ ሸንሀት ጅማዕ ለቦም ውላድ ህለው።እንዴ ፈተው እንዴ ኢገብኦ ዲብ ነፍሶም ነቃሰት ሰበት ህሌትቱ።ከዜድ ሐበት- አሰውዳ እቡ ትነፋዕነ ምን ገብእ ለናይ ጅማዕ ሽዑርነ ለሐሶሴ ወለ ዘርእ ውላድ ህዬ፡ ዲበ ትትሐዜ ደረጀት ወቅያስ ክም በጼሕ ልትሐበር።ክምሰሌሁመ፡ ሐበት- አሰውዳ፡ዱረት ደም ነዝም ወድድ ለትፈናተ ባክቴርየ ሕማማት ለትቀትል ማደት በ።እብ ተውሳክ ዲብ ለገብአ ክፋል ገሮብነ፡መጺጸት ህሌት ምን ገብእ፡ለለአመጸነ ለሀለ ክፋል ገሮብነ፡እበ ዜድ ሐበት-አሰውዳ ንሽመቱ፡ንድዐኩ ወንርሀቡ።ለመጺጸት እግል ተአንቅሰ አውመ እግል ተአብጥረ ምኒነ ክም ትቀድር፡ለእብ ክሱስ መንፈዐት ሐበት-አሰውዳ ድራሳት ለወደው ዑለማእ ዓፍየት ወአስርየት ለሐብሮ።
ዜድ ሐበት-አሰውደ ዲብ ሳረዮት ወመዳፈዐት ለትፈናተ ሕማም ለህሌት እግሉ ፍገሪት ዐባይተ። ዜድ ሐበት-አሰውደ እግል ጭገር ሰኒ ክምሰልቱ ልትሸረሕ።ዲብ ጭገር አውመ ጅልድ ረአስነ ለልትረኤ ለትፈናተ ሕማማት ክምሰል ከረ ፈላቂት፡ፎሮፎር ሐላት ወለመስሉ ሕማማት ምኑ ክም ዳፌዕ ወሳሬ ለበሐስ ለወደው ዕለማእ ዓፍየት አዳም ወዕልም አስርየት ለሐብሮ።ለዜድ ሐበት-አሰውዳ እግለ ጭገርነ እንዴ ኢገብእ ለቀርበትነ እግል ንድዐክ እቡ ብነ።እግልሚ ለጭገር እግል ልትዓፌ ገብአ ምን ገብእ ለዲበ በቅል ቀርበትነ ዑፊት እግል ትግባእ በ።ለዲብ ቀርበትነ ለሀለ መፋርቅ እግል ልፋቴሕ ወለዐለ ዲብነ ሕካክ ልግባእ፡ ፈንጋስ፡ሐላት፡ፎሮፎር ወለገብአ ሕማም ቀርበት እግል ለሓዬ ቀድር።እት ረአስ እሊመ ዜድ ሐበት-አሰውዳ፡ እግለ እብ ሐፋነት ጸሓይ መደረት ለጀሬት ዲበ ቀርበትነ፡ዲበ ናይ አማን ሕብረ እግል ልብለሰ ቀድር።እሊ ህዬ እብ ገበይ ሲቶ ወሸሙት ንትነፋዕ እቡ በህለት ቱ።እትለ እግል ነኣምረ ለብነ ላኪን፡ዜድ ሐበት-አሰውዳ እግል ኩሉ ጅንስ ሕማም ቀርበት ሳሬ ለበህለት ኢኮን።እት ለገብአ ለረክበነ ሕማማትመ ሐኪም ኢትትረው እንብል ይህሌነ።ለመንፈዐት ሐበት-አሰውዳ ብዝሕት ሰበትተ ንጀርቡ ሌጠ እንብል ህሌነ።እሊ ለናይ ሰብ መቅደረት ዓፍየት ፍሑሳት፡ምክር ወሐብሬ ዲብ አካኑ እንዴ ሀለ በህለት ቱ።ከራድኢት ሻፍገት ለተአትሐዝዩ ወዓፍየትነ እት ብቆት ለከሬ ሕማማት ኢገብአ ምን ገብእ፡ ጀርቤ ሐበት-አሰውደ ሰኔተተ።ለራድኢት ሻፍገት ለተአትሐዝዩ ሕማማት ላኪን አስክ መንደርሐካይም እግል ንርዳእ እቡ ብነ።
እብ ተውሳክ ዜድ ሐበት-አሰውደ፡ እግል ሳረዮት መትዐቃድ አስራር ደም ክም ሳሬ ልትሐበር።እብ ጭብ ናይ አስራር ደም ወሐፋሰትለ ደምነ፡እግል ልትከራዕ አውመ አስራርነ እግል ልትዐቀድ ቀድር።ከዜድ ሐበት-አሰውደ እግል እሊ መዓቅድ እሊ ክም በርብሩ ልትሸረሕ።እሊ ህዬ እብ ሰበብ ኮልስትሮል ለሳድፍ ልግባእ ወእብ ሐፋሰት ደም እግል ልርከበነ ቀድር። ከዲብ አቅጠኖት ሐፋሰት ደም ሐበት-አሰውዳ ተረተ ዐባይ ክምተ ለባሕሲን ለሐብሮ።ዲብ ሙአሰሳት ዓፍየት እግል አቅጠኖት ደም ለልትሀየብ (ብላክ ሲናት) ለልትበሀል ደወ ልትሀየብ።ኩሉ ለእነስኡ አስርየት መንፈዐት ወመደረት ክምሰልቡ እሙርቱ።ከለ ደወ እንዴ ይእነስእ ለዜድ ሐበት- አሰውደ ምን ንትነፋዕ ምነ መደረትለ ለልትሀየበነ ደወ እግል ንድሐን እንቀድር በህለት ቱ።እብ ሐካይም ለትቀረረ እግልነ ስራይ ዐለ ምን ገብእ ላኪን፡ እምበል አትካራም እግል ንንስኡ ብነ። ምናተ ምነ መደረት ለቡ ስራይ መሳኔዕ ለመደረት ለአለቡ ስራይ ጠቢዒ እቡ ምን ንትነፋዕ ለሔሳቱ።
ዜድ ሐበት-አሰውዳ እምበል እሊመ፡ ዲብ አቅለሎት መጺጸት እንተሃባት አንያብ፡ ምራቅነ ዶል በዜሕ ወንትቦለል፡ዲብ ለትፈናተ እብ ሰበብ እንተሃባት ወዉርበብ ለመጽእ ሕባጥ፡ አንቲ ፓራሳይድ በህለት ድድ ባልዒን ከብድ፡ ዲብ መሓረበት ኮልስትሮል፡አው ዲብ አውሐዶትለ እት ነፍስነ ለልትከለቅ መደረት ዓፍየት ለሰብብ ሽቤሕ፡ ምለዐል ኩሉ ህዬ ለብላክ ሲድ ለእምብሉ ዜድ ሐበት-አሰውደ፡ ምስል ዜድ ቱም እንዴ ሓበርነ ምን እነስኡ ዲብ መዳፈዐት ወሳረዮት ሕማም ሰረጣን፡ሕዴ ዘርእ ውላድ ለቦም ሰብ ልግብኦ ወአንስ፡ እግለ ዘርእ ውላድ እንዴ አብዘሐ ወአትሐሶሰ ክም ነፈዖም፡ እብ ፍንቱይ ዲብ አንሳት እት ወቅት ሔድ አውመ ደውረት ደም ለትሳድፈን መጺጸት አጥባይ ዶል ተሀሌ፡ እበ ዜድ ሐበት-አሰውደ ምን ሸምታሁ ለመጺጸት ክም ትበጥር አውመ ትነቅስ ለሰብ መቅደረት በሓስ አስርየት ሸርሖ። ምናተ ለእግል ልዕመሰ ለለሐዝየ ወዐመሲ ኩሉ-ኩሉ ዜድ ሐበት አሰውደ እግል ልስተያሀ አው ህዬ እንዴ ወጋእያሀ እግል ልቃሕማሀ ወልምጨራሀ አለበን። እግልሚ ዲብ ዐመሲ ወአዜ እግል ልዕመሰ ለለሐዝየ እ’ማት መደረት ሰበትበ እግል ልንሰኣሀ አለበን። ምን ምለዐል ላኪን እበ ዜደ ቀርበተን ምን ሻምተ መደረት ክም አለቡ ልትሐበር።
ክምሰል እሊ እተ ለሐልፋ ክፋል ልግባእ ወእትሊ ናይ ዮም ክፋል፡መንፈዐት ዜድ ሐበት-አሰውደ ብዝሕት ተ።(ሉኪንያ) ለልትበሀል ጅንስ ሕማም ሰረጣን ደም ሀለ።እሊ ሕማም እሊ ህዬ ለበዝሐ ወቅት ዲብ አጀኒት ለልትረኤቱ።ከዜድ ሐበት-አሰውዳ እግል እሊ ሉኪንየ ለልትበሀል ጅንስ ሰረጣን ደም እግል ለሓይዩ ክም ቀድር ለባሕሲን እኩዳም ህለው። እሊ ላኪን እበ ለትትሐበር ገበይ ራትዐት ምን እነስኡ ቱ። ለሐብሬለ ገበይ ወቅያስ ንስአቱ ህዬ፡ እግል ኑኡሽ ልግባእ ወእግል ዐቢ፡ክምሰለ ዘመናይ አስርየት መደረት ሰበት አለቡ፡ አስቦሕ፡ አደሐ ወምሴ፡ሐት ሐቴ መንከት ሻሂ ምን ዜድ ሐበት-አሰውዳ ዶል እነስእ ለምን እሊ ጅንስ ሰረጣን እሊ እግል ንሕዬ ለሀለ እግልነ በክት ሰኒ ዐቢቱ።
ዜድ ሐበት-አሰውደ ዲብ ሕማም ኤፐለፕሲ አው ቀዛል ወየባሰት ቀነቅሽመ ሰኒቱ። ዲብ ንስአቱ ላኪን፡ ምነ ቀደም እለ እንሸርሑ ለጸነሕነ ሰለስ ዶል ዲብ ምዕል፡ለሕማም ወዲቅ ወየባሰት ቀነቅሽ ለቦም አንፋር፡ ዲብ አምዕል 4 መዶል ወእብ ሲቶ፡ እብ ሐሪጩ ቅሒም ወእብ ምጫር ፍሬሁ እግል ልንስእው ቦም። እት ረአስ እሊመ እግል ልትሸሞቱ ቀድሮ።
ናይ ጋስትራይት በህለት እስትሞኮ አልሰር አውመ መትሰንዳር ወጸሌዕ ከርሸት ለቦም፡ ሕማም ኤች-ፓይሎሪ ለልትበሀለ እንተሃባት ባክቴርየ ከርሸት ለሕሙማም፡ እሎመ ሐበት-አሰውደ እንዴ ወግአወ እብ ሐሪጭ ምን ልቅሑመ ሰዳይተ ሰኒ ዐባይተ። እብ ዜድ እግል ልንስእዉ ቀድሮ ላኪን ክም ሐሪጭ ምን ልቅሑመ ዝያደት ፍገሪት ሻፍገት ክምበ ልትሐበር።ዲብ ሳረዮት ሄፓታይትስ B ወሄፓታይትስ C ለእምብሎም አጅናስ ሕማም ስፌር፡ እብ ፍንቱይ ለስፌር ጻዕደ ለእምብሉ ስራይ ለአለቡ ሕማም ድቁብቱ ልትበሀል። እምበል ሸክ ለናይ ስፌር ጻዕደ ቫይረስ ዲብ ዓፍየት አዳም ለሰብበ መደረት ሰኒ ዐባይተ።ምናተ ሐበት-አሰውዳ እግል ትሳርዩ ክም ትቀድር ለዕለማእ ወድሖ። እሊ ህዬ ምስላመ ሐበት-አሰውደ እብ ሐካይም ለልትቀረር እግልነ ስራይ እንዴ እነስእ በህለት ቱ።ዜድ ሐበት-አሰውደ ሕማም ስፌር ጻዕደ አውመ ሄፓታይትስ C 100 ምን% ክምሰል ሳርዩ ለባሕሲን ለአክዶ። ከሕና ለባሕሲን ወሐካይም ለልቡሉ በሀል ዲብ አካኑ እንዴ ሀለ፡ እሊ ለትባህለ ሕማም ስፌር ጻዕደ ለቦም አንፋር ሰአየት እንዴ ኢበትኮ እብ ፍዕል ምን ጀሩቡ ለሔሳ ቱ። ነስእዉ እንዴ ህለው ላኪን፡ እብ ዜድመ ደሐንቱ ላኪን ለሔሰት ወለሸፍገት ፍገሪት፡ እንዴ ደቀቅናሁ እብ ሐሪጭ ምን እንቅሕሙ ልትሐሬ።
ዜድ ሐበት-አሰውደ እምበል እሊመ፡ እግለ ሕማም ዐነጽብ፡ መጺጸት አብራክ፡ መጺጸት ዔጻት፡ መናክብ ወለትፈናተ አፍካክ ለቦም አንፋር፡ ሰለስ ሳምን እንዴ ኢለአትካርሞ፡ ዲብ ምዕልከ አስቦሕ፡ አደሐ ወምሴ ሐት-ሐቴ ምንከ ሻሂ ምን ዜድ ሐበት-አሰውደ ምን ነስኦ፡ ኔፍዓይ ክምሰልቱ ልትሐበር። ምናተ ትሸባህነ ወሐዬነ እንዴ እምቤ እግል ነአትካርሙ አለብነ። እብ ተውሳክ ዜድ ሐበት-አሰውደ፡ ዲብ ሐናት በህለት እንተሃባት ሐለቅም ክም ሳሬ ልትሸረሕ። እትሊ ሕማም እሊመ ለዜድ እንሰትዪ አውመ መድመደት እንዴ ወዴናሁ ለሀለ ዲብነ ሕባጥ ሐናት ምን ነሐጽብ እቡ ዲብ ሐዮትለ ሕማም መንፈዐት ዐባይቡ።
እሊ ኩሉ መንፈዐት ናይ ሐበት-አሰውዳቱ። ላኪን፡ ሐኪም ኢትትረአው፡ ዕያዳት ኢቲጊሶ፡ ለትነስእዉ ለጸናሕኩም አድውየት አትካርሞ ከዲቡ ሌጠ ረክዞ ይእምብል። እተ ለሀለ ዲብነ ሕማማት ምክር፡ ሐብሬ ወሰብ መቅደረት ዓፍየት ንስእዉ ለቤለውነ አስርየት እንዴ እነስእ፡ እብሊ ለትሸርሐ አግቡይ ሐበት-አሰውደ እግል ንትነፋዕ እበ ብነ።